የቴዲ አፍሮ የሰርግ ስነ ስርአት በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው

የቴዎድሮስ ካሳሁን የሰርግ ስነ ስርአት በዛሬው እለት የተከናወነ ሲሆን ፣በዚሁ ሰርግ ላይ ከአሜሪካ እና ከአውሮጳ የሄዱ የቅርብ ወዳጆቹ እንደተገኙ መረጃው ያመለክታል  በልዩ ሁኔታ ያከበረው ይህንን ሰርጉን ያከበረው ቴዲ አፍሮ ከፍተኛ የደስታ ስሜእት ነበረው ሲሉ ጓደኞቹ ለማለዳ ታይምስ የገለጹ ሲሆን ፣ይህም ለራሱ እና ለቤተሰቦቹ ኩራት ነው በማለት አወድሰውታል ። የሰርጉ ስነ ስርአት በዛሬው እለት ማለትም ሃሙስ ቀን ለምን ሊሆን ቻለ የምሚሉ ወገኖች እንደነበሩም የሰማን ሲሆን። የቴዲ አፍሮ ሰርግ ባልተለመደ መልኩ ለምን ሐሙስ ቀን እንዲሆን መወሰኑን  የታዲያስ አዲስ አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን
መረጃውን  ገልጿል::

የቴዲ አፍሮ የሰርግ ስነ ስርአት በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው

መስከረም 17 እና ቴዲ ብዙ ታሪክ አላቸው:-
1ኛ. የመስቀል በዐል ስለሆነ
2ኛ. አባቱ የተቀበረበት ዕለት ስለሆነ
3ኛ. የቴዲ እናት ልደት ነው
4ኛ. የእውቁ ድምጻዊ የዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ልደት ስለሆነ ነው::
ከቴዲ ሚዜዎች መካከል ሸዋንዳኝ ሀይሉ; የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ቴዲ ባሪያው: ሀይልዬ ታደሰና የእውቋ
ሞዴል ሊያ ከበደ ወንድም ኤርሚያስ ከበደ ይገኙበታል:: ሆናቸው  ኤርሚያስ ከበደ በአቡጊዳ ባንድ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ካላቸው ውስጥ አንዱ ነው በቤዝ ጊታር ተጨዋችነትም ይታወቃል ፣ኤርሚያስ ከሚኖርበት ቺካጎ ለኮንሰርት ጉዞ እና ለሰርጉ ዝግጅት በማለት ከአራት ወራት በፊት ቀደም ብሎ ወደ ኢትዮጵያ እንደተጓዘ መረጃዎቻችን ከማለዳ ታይምስ ያትታሉ::  በአጠቃላይ ከቴዲ በኩል ሰባት እና በሚስቱም በኩል 7 ሚዜዎች ይኖሩዋቸዋል:: ከአምለሰት ሚዜዎች መካከል የኤፍሬም ታምሩ ልጅ ቤዛ ኤፍሬም ታምሩ አንድ ልጁ ትገኝበታለች::የሚገርመው የምሳ ፕሮግራሙ  በብዙዎች ዘንድ ቴዲ በሸራተን ሆቴል ዝግጅት ማካሄድ የለበትም የሚል የተቃውሞ ቃላትን ሲወራወሩ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የምሳ ፕሮግራሙ እና የፎቶ ፕሮግራም  እዚያው መፈጸሙ ተገልጾአል  ከዚህ በፊት በሸራተን አዲስ  ዝግጅቱ እንደሚከናወን የማለዳ ታይምስ አዘጋጅ መጠቆሙ ይታወሳል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *